ዊኪ-መዝገበ-ቃላት የባለ ብዙ ቋንቋው ዊክሽነሪ የአማርኛ ዝርያና የ ዊኪፒዲያ ነፃው መዝገበ-ዕውቀት እህት መርሃ ግብር ነው። ዓላማውም ሁላችንም በመተባበር አንድ ክፍት ነፃና ሁሉም ሰው ያለ ምንም ገደብ ሊጠቀምበት የሚችል መዝገበ-ቃላትን መድረስ ነው። ይህ የኣማርኛ ዊኪ-መዝገበ-ቃላት በማርች 23 2006 ተጀምሮ በአሁኑ ሰዓት 2,456 ገጾችን ይዟል። አንድ ገጽ የአንድ ቃልን ምንጭ፣ ሂደታዊ ታሪክን፣ የቀድሞና ወቅታዊ አጠቃቀምን፣ ተዛምዶን፣ የአጠቃቀም ምሳሌን፣ ተጨማሪ ተጠቃሽ መረጃዎችን፣... ወዘተርፈ ይይዛል።
ይህ መዝገበ ቃላት አማርኛን እንደ ማዕከላዊ መነሻ ቢያደርግም በዓለም ላይ ያሉ ቋንቋዎችን ሁሉ ቃላት ማካተት ይቻላል። ይህ ከላይ ሲመለከቱት አስቸጋሪና መዝገበ ቃላቱን ስርዓት የሚያሳጣው ሊመስል ይችላል። ይህ የሚመስለን በባሕላዊው ኅትመት ላይ የተመሠረተ የመዝገበ ቃላት አጠቃቀምን ስለምናስብ ነው። የዓለም ቋንቋዎችን ሁሉ በአንድ መጽሐፍ ላይ እናስቀምጥ ብንል የማይቻል ነው። ለመቀምር (Computer) ምስጋና ይግባውና የዕውቀትና የጊዜ ገደብ ካልሆነ በስተቀር ከላይ የተጠቀሰው ዓይነት ገደብ እዚህ ላይ አይኖርም።
የሚያውቁት ቋንቋ ካለ፥ ኦሮምኛ፣ ከምባትኛ፣ ኑዌር፣ ወላይትኛ፣ አገውኛ፣ ትግርኛ፣ ጃፓንኛ፣ ህንድኛ፣ ቻይንኛ፣ ፈረንሳይኛ፣ ኖርዌጅኛ፣... ወዘተርፈ ቃሉን ጽፈው ከየት እንደመጣ፣ ትርጉሙን፣ ተጠቃሽ መረጃዎችን... ወዘተርፈ ማስቀመጥ ይችላሉ። የየትኛውንም ቃል የአማርኛ ትርጉም ለማወቅ የፈለገ ተጠቃሚ ሁሉ ወደዚህ መጥቶ ማየት ይችላል ማለት ነው። በተለይ ይህ በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚገኙ ቋንቋዎች ቃላት እንደ ማከማቻና አንዱ ከአንዱ ጋር ያለውን ግንኙነት እንደማሳያ ሊያገለግል ስለሚችል የሚያውቁትን ቃላት በሙሉ በማስገባት ትርጉማቸውን ያስቀምጡ።
|