Jump to content

እምቢልታ

ከWiktionary

እምቢልታ የአገው ብሄረሰቦች ለሰርግ ማጀቢያነት የሚጠቀሙት የትንፋሽ መሳሪያ ነው። እምቢልታ የጃዊ፣ዳንጉር እና ቋራ ወረዳዎች መለያ ከሆኑት ባህላዊ የትንፋሽ መሳሪያዎች ውስጥ አንዱ ነው። እምቢልታ የሚሰራው ከቅርቀሃ ሲሆን በቁጥር ስድስት ናቸው። 1.ቹዋ(1) 2.ኩሊላ(2) 3.አይማ(1) 4.ዳራ ዙሪ/አውራ(2)ይባላሉ ለሰርግ የሚዜሙ 4ቱ ዜማዎችም 1ኛ.ጊኚ፦ሙሽራው ጉዞ ላይ እያለ 2ኛ.ታምና፦ ሙሽራው ሙሽሪት ቤት ሲደርስ 3ኛ.ታጋና ባታና ፦ ሙሽሪት ሲረከቡ 4ኛ. ድኮርዝኝ፦ ሙሽሮች በበቅሎ/በፈረስ ተጭነው ሲሄዱ