Jump to content

አባል ውይይት:አብርሃም

Page contents not supported in other languages.
ርዕስ ጨምር
ከWiktionary
Latest comment: ከ14 ዓመታት በፊት by አብርሃም

በንግግራችን አማርኛን በእንግሊዝኛ ማጀብ ለምን? እስከመቼ?

በጣም የሚገርመኝ ጉዳይ አማርኛ ስናወራ እንግሊዘኛ ቃላት እንጨምራለን። ጥርት ያለ አማርኛ ብቻ የሚያወራ ሰው እየናፈቀኝ ነው። ይህ ነገር በአብዛኛው ሰው በምሁራን ሳይቀር የሚስተዋል ነገር ነው። ችግር አለበት/ የለበትም የሚለውን ተወያዮች ሃሳብ ይሰጡበታል። ግን አማርኛችን እንግሊዝኛ ሳያጅበው ብቻውን በሙሉነት ለማግባባት ምን ያንሰዋል? ችግራችን ምንድን ነው? (አስተያየት ለመስጠት፡ ከዚህ ገጽ ከላይ ፣አርም፡ የሚለውን ቁልፍ በመጫን ሃሳብን መጻፍ ይቻላል። ሲጨርሱም ከታች ገጹን አስቀምጥ የሚለውን መጫን።)

እኔ እንደሚመስለኝ የእንግሊዝኛ ቃላት የሚጨመሩት ለብዙ ሀሳቦች የእግሊዝኛው ቃል በስፋት ስለምንጠቀመው አእምሮ ላይ ኖሮ እንግሊዝኛ የምንናገርም አይመስለንም። Elfalem 03:42, 21 ጁላይ 2010 (UTC)Reply


ሠላም፡ ኤልፋልም (ስምህን/ሽን አሳስቼ ካልሆነ)። ስለ አስተያየቱ አመሰግናለሁ። በአማርኛችን ሙሉ ሃሳባችን ለመግለጽ የቃላት እጥረት አለ ማለት ነው? እንደዛ ከሆነ እንግሊዝኛ የማያውቁ የአማርኛ ተናጋሪዎች በሙሉነት እየተግባቡ አይደለም ልንል ነው? ቢሆንስ ደግሞ መፍትሔው እንግሊዝኛ መቀላቀሉ ነው ወይ?

የቃላት እጥረት ለአንዳንድ ሁኔታዎች አለ፣ ለሌሎች ደግሞ የለም። ለምሳሌ አንዳንድ ትምህርት ነክ ቃላት ለብዙ ሰዎች የሚታወቁት በእንግሊዝኛ ነው (በሒሳብ ላይ ratio የሚባለው "ውድር" ነው ግን ይህን ቃል እስከ እዚህ ዓመት ድረስ እንደነበረ እኔም አላወቅኩም ነበር፣ Mercury the planet በአማርኛ "አጣርድ" ነው የሚባለው)። ሌላ ጊዜ ደግሞ ችግሩ የሚከሰተው በሥልጣኔ ምክኒያት። በሳይንስና በሌላ ዘርፎች የረቀቁ አገራት ያላቸው ቃላት የአማርኛ አቻ የላቸውም። ለምሳሌ magnet, magnetic, stratosphere, Cenozoic Era የአማርኛ ትርጉም ያላቸውም አይመስለኝም። እኛ በአማርኛው ውክፔዲያ ላይ በትብብር ስንሰራ ይህ አቢይ ችግር ነው። ለቀን ተቀን ንግግር ግን በበቂ በላይ አማርኛ ቃላት አሉ፤ ባንጠቀማቸውም። ግን ተማሪና አስተማሪ ለመግባባት እንግሊዝኛ ቃላት ከመጠቀም ሌላ አማራጭ የለም (አዲስ ቃላትን ካልመሠረትን በቀር)። Elfalem 23:36, 21 ጁላይ 2010 (UTC)Reply

አሁንም ስለመልሱ አመሰግናለሁ። በሳይንስና በቴክኖሎጂ ቃላት ረገድ ካየነው፡ ልክ ነው። ብዙ የቃላት እጥረት አለ፡፡ ይህም ቴክኖሎጂው ያመጣው እንደመሆኑ መጠን የአማርኛችን ችግር አይደለም። ነገር ግን አማርኛችን ከዘመኑ ጋር ይሄድ ዘንድ እንዲህ ዓይነት ሥራዎች በጣም ያስፈልጋሉ። በዚህ ነጥብ ማከል የምፈልገው ከዛሬ 12 ዓመት በፊት በኢትዮጵያ ቋንቋዎች አካዳሚ የተዘጋጀ የሳይንስና ቴክኖሎጂ መዝገበ ቃላት መኖሩን በቅርቡ ከድረ-ገጽ አግኝቼአለሁ። በዚህ አድራሻ ይገኛል። www.good-amharic-books.com ከሚለው ዋና ገጽ- መጻሕፍት-ሪፈረንስ መጻሕፍት በመግባት ማግኝተ ይቻላል፡ እኔ ዋናው ጥያቄየ በመደበኛ ንግግራችን ላይ አማርኛ ቃላት እያለ በእንግለዝኛ ማጀብ ለምን? እስከመቼ? የሚል ነው። ይህ ነገር አማርኛችን የባሰ እየገደለው/እያጠፋው እንዳይሄድ እሰጋለሁ። በብዙ ምሑራንና ወጣቶች ስታይ የሚነገረው አማርኛ ሳይሆን አማርኛዊ እንግሊዝኛ ይመስላል። --አብርሽ 09:01, 22 ጁላይ 2010 (UTC)Reply

ለውይይቱ እኔም አመስግናለሁ። ስለ የሳይንስና ቴክኖሎጂ መዝግበ ቃላት መኖሩን በዚ ዊክሽነሪ ተረድቼአለው። good-amharic-books.com በጣም ጠቃሚ የሆኑ ብዙ መጻሕፍትን ይዟል። ስለ ዋና ጥያቄህ፣ ለምን ለሚለው እኔ የሚመስለኝ የእግሊዝኛ ባሕል በመዝኛኛነት አኳያ በጣም ኢትዮጵያ ውስጥ ስር ሰድዋል። እንግሊዝኛ መቀላቀል እንደ ሥልጣኔ የሚቆጠር ይመስለኛል። እስከመቼ ለሚለው፣ ንፁህ የአማርኛ ቋንቋን አጥብቆ የሚያስተምር በሰፊ ምንባብ የሚያገኝ ነገር እስከሚኖር ይመስለኛል። ለዚህ ነው እኔና ሌሎች አባሎች የአማርኛ ውክፔዲያ እንዲስፋፋና እንዲዳብር የተቻለንን ጥረት የምናረገው። አቅሙ ቢኖረኝ፣ በአማርኛ ዊክሽነሪ ላይም ብሳተፍ ደስ ይለኛል። Elfalem 02:53, 23 ጁላይ 2010 (UTC)Reply

በእውነት ትኩረት ሰጥተው እየተወያየን በመሆኑ በጣም ደስ ብሎኛል። እንግዲህ ከተግባባን ሌሎችም በዚህ ሃሳብ እንዲወያዩ የተቻለንን ጥረት ብናደርግ ባይ ነኝ። በበኩሌ ይህን ድረ-ገጽ ካገኘሁበት ቀን ጀምሮ ለጓደኞቼ እየተናገርኩ ነው። ግን በዚህ በአማርኛ ዊክሽነሪ ላይ ስንት አባላት አሉ? ምን ያህሉስ ይሳተፋሉ? የዚህ መረጃ እንዴት ይገኛል? ለምሳሌ በፌስቡክ በአማርኛ ላይ ብዙ አባላት ቢኖሩም ብዙዎቹ አይሳተፉም። ያሉትም ቢሆን ደህና ውይይት ያደርጋሉ፡፡ እዚህ ጋ ግን አንደዚህ አላየሁም። ምንድን ነው ችግሩ? ወዳነሳሁት ርእስ እመለሳለሁ።--አብርሽ 08:42, 26 ጁላይ 2010 (UTC)Reply

ለጓደኞችህ በመናገርህ እናመሰግናለን። በዚህም ሆነ በማንኛውም ቋንቋ ዊክሽነሪ ወይም ውክፔዲያ ላይ Special:statistics ብለህ የፍለጋ ሳጥን ውስጥ ብታስገባ ዝርዝር መረጃ ይገኛል። በመቶዎች የሚቆጠሩ አባሎች ቢኖሩም፤ እኔ እንዳየሁት ከሆነ ከአንድ የቦት አባል (computer robot) በስተቀር ብዙ እንቅስቃሴ በዚህ ዊክሽነሪ ላይ የለም። እኔና ሌሎች አባሎች የምናተኩረው በአማርኛው ውክፔዲያ ላይ ነው። አንድ የውክፔዲያ ወይም ዊክሽነሪ የብዕር ስም (account) ካለህ ማንኛውም ቋንቋ ውክፔዲያ ወይም ዊክሽነሪ በዚያ ብዕር ስም ማረም ይቻላል። የአማርኛው ውክፔዲያ ወደ አምስት የሚሆኑ በጣም ትጉህ የሆኑ (በየቀኑ ወይም በየሳምንቱ ሁለቴ ወይም ሶስቴ የሚያርሙ) አባሎች አሉት። አልፎ አልፎ የሚያርሙት ደግሞ በዛ ይላሉ። ፌስቡክ የጓደኛና የቤተሰብ መወያያ ስለሆነ ብዙ ተሳትፎ መኖሩ አይገርምም። ብዙ ሰዎች ግን የውክፔዲያ ወይም ዊክሽነሪ ጥቅም አይታያቸውም። Elfalem 03:18, 27 ጁላይ 2010 (UTC)Reply

በቅድሚያ በሥራ ብዛት ስለጠፋሁ ይቅርታ። እንደኔ ሃሳብ መረጃውን የማግኘት ችግር ይመስለኛል ብዙ ሰዎች እንዳይሳተፉ ያደረጋቸው። ምናልባት በማያያዣ (ሊንክ) መልክ እንደፌስቡክ እና በሌሎች ድረ-ገጾች ላይ ማስቀመጥ አይቻልም ወይ? የሚያስከፍሉ ይኖሩ ይሆናል። ግን በነጻ እና የማሕበረሰብ በሆኑ ብዙ ተመልካች ባለባቸው ቦታዎች ከአጭር ገለጻ ጋር በማያያዣ መልክ ቢቀመጥ ብዙ ሰው/ አባላት ይመጣሉ የሚል እምነት አለኝ።--አብርሽ 12:05, 2 ኦገስት 2010 (UTC)Reply