የሐረጎች ዝርዝር1

ከWiktionary
አማርኛ እንግሊዝኛ
ይህ ዓለም ይጠፋል? Will the world be destroyed?
መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ዓለም ፍጻሜ እንደሚናገር ታውቅ ይሆናል። You probably know that the Bible speaks of the end of the world.
ታዲያ መጽሐፍ ቅዱስ ይህን ሲል የሰው ዘር ስለሚጠፋበት ጊዜ መናገሩ ነው? Does the Bible say that the end is near?
ምድራችን ሕይወት አልባ እንደምትሆን ወይም ሙሉ በሙሉ እንደምትጠፋ መናገሩ ነው? Does it mean that our planet will be lifeless or completely destroyed?
መጽሐፍ ቅዱስ፣ የዓለም ፍጻሜ ሁለቱንም ነገሮች እንደማያመለክት በግልጽ ይናገራል። The Bible clearly states that the end of the world does not mean either.
የማይጠፋው ምንድን ነው? What does not perish?
የሰው ዘር Mankind
መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል? What does the Bible say?
አምላክ ምድርን መኖሪያ እንድትሆን እንጂ ለከንቱ [አልፈጠራትም]። ኢሳይያስ 45:18 God did not create [the earth] simply for nothing ; but formed it even to be inhabited. ; - Isaiah 45:18
ምድራችን Our Earth
መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል? What does the Bible say?
ትውልድ ይሄዳል፤ ትውልድ ይመጣል፤ ምድር ግን ለዘላለም ጸንታ ትኖራለች። መክብብ 1:4 Generation goes on; Generations come; But the earth is standing even to time indefinite.  ;- Ecclesiastes 1: 4
ይህ ምን ማለት ነው? What does this mean?
መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚናገረው ምድር መቼም አትጠፋም፤ ምንጊዜም የሰው ልጆች መኖሪያ ሆና ትቀጥላለች። According to the Bible, the earth will never be destroyed; It will always be the home of mankind.
ታዲያ የዓለም ፍጻሜ ሲባል ምን ማለት ነው? What, then, is the end of the world?
መጽሐፍ ቅዱስ፣ መጪውን የዓለም ፍጻሜ በኖኅ ዘመን ከተከሰተው ነገር ጋር ያመሳስለዋል። The Bible likens the end of the world to the time of Noah.
በዚያን ጊዜ ምድር ;በዓመፅ ተሞልታ  ; ነበር። The earth was then filled with violence. ;
ኖኅ ግን ጻድቅ ሰው ነበር። But Noah was a righteous man.
ስለዚህ አምላክ ክፉ ሰዎችን በውኃ ሲያጠፋ ኖኅንና ቤተሰቡን አዳናቸው። So when God destroyed the wicked in the water, he saved Noah and his family.
መጽሐፍ ቅዱስ ያኔ ስለተከሰተው ጥፋት ሲናገር እንዲህ ይላል፦ በዚያ ጊዜ የነበረው ዓለም በእነዚህ ነገሮች ጠፍቷል። Regarding the catastrophe, the Bible states: At that time the world Lost in these things.
ይህም የሆነው መላዋ ምድር በውኃ በተጥለቀለቀች ጊዜ ነው። ; That was when the whole earth came to be flooded.  ;
ያኔ የነበረው ዓለም የጠፋው በዚህ መንገድ ነው። This is how the world at that time was destroyed.
ሆኖም የጠፋው ምንድን ነው? But what is missing?
ምድር ሳትሆን በምድር ላይ የሚኖሩ ክፉ ሰዎች ናቸው። They are the wicked, not the earth.
ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ዓለም ፍጻሜ ሲናገር ምድር እንደምትጠፋ መናገሩ አይደለም። So when the Bible speaks of the end of the world, it does not mean that the earth will be destroyed.
ከዚህ ይልቅ የሚጠፉት በምድር ላይ ያሉ ክፉ ሰዎችና እነሱ ያዋቀሩት ሥርዓት ነው። Instead, they will be destroyed, and the wicked will be destroyed.
የሚጠፋው ምንድን ነው What is missing?
ችግር እና ክፋት Trouble and evil
መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል? What does the Bible say?
ለጥቂት ጊዜ ነው እንጂ ክፉዎች አይኖሩም፤ በቀድሞ ቦታቸው ትፈልጋቸዋለህ፤ እነሱ ግን በዚያ አይገኙም። Just a little while longer, and the wicked one will be no more; You will find them in their former place, But they are not there.
የዋሆች ግን ምድርን ይወርሳሉ፤ በብዙ ሰላምም እጅግ ደስ ይላቸዋል። መዝሙር 37:10, 11 But the meek ones themselves will possess the earth, And they will indeed find their exquisite delight in the abundance of peace.  ;- Psalm 37:10, 11
ይህ ምን ማለት ነው? What does this mean?
በኖኅ ዘመን የተከሰተው የጥፋት ውኃ፣ ክፋት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንዲወገድ አላደረገም። The Deluge of Noah's day did not end with an end to the present wicked system of things.
ከጥፋት ውኃው በኋላ፣ ክፉ ሰዎች እንደገና የሌሎችን ሕይወት መራራ ማድረጋቸውን ቀጠሉ። After the Flood, the wicked began to make others bitter.
በቅርቡ ግን አምላክ፣ ክፋትን ጠራርጎ ያስወግዳል። But God will soon do away with evil.
በመዝሙር መጽሐፍ ላይ እንደተጠቀሰው ክፉዎች አይኖሩም። ; As the book of Psalms states, the wicked one will be no more. ;
አምላክ ክፋትን የሚያስወግደው እሱ ባቋቋመው መንግሥት አማካኝነት ነው፤ የአምላክ መንግሥት፣ ከሰማይ ሆኖ ጻድቅ ሰዎችን የሚያስተዳድር ዓለም አቀፍ መንግሥት ነው። God will eliminate evil by means of his Kingdom, God's Kingdom is a real government, one that will rule over the righteous from heaven.
አሁን በዓለም ላይ ያሉ መንግሥታት፣ የአምላክን መንግሥት አገዛዝ ይቀበላሉ? Will the governments of this world accept the rulership of God's Kingdom?
መጽሐፍ ቅዱስ እንደማይቀበሉ ይናገራል። The Bible says no.
እንዲያውም የአምላክን መንግሥት በመቃወም የሞኝነት ድርጊት ይፈጽማሉ። In fact, they are acting foolishly against God's Kingdom.
ውጤቱስ ምን ይሆናል? What will be the result?
የአምላክ መንግሥት፣ ሰዎች የሚያስተዳድሯቸውን መንግሥታት በሙሉ ያጠፋል፤ እሱም ብቻውን ለዘላለም ይቆማል። ; God's Kingdom will destroy all human governments; "He alone will stand forever."
ሆኖም ሰዎች ያቋቋሟቸው መንግሥታት መጥፋት ያለባቸው ለምንድን ነው? But why do governments have to be destroyed?
የሰው አገዛዝ መጥፋት አለበት Human rule must be abolished
መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል? What does the Bible say?
የሰው ልጅ አካሄዱን እንኳ በራሱ አቃንቶ መምራት አይችልም። ;;ኤርምያስ Humans cannot even direct their own steps. ; Jeremiah
ይህ ምን ማለት ነው? What does this mean?
ሰው ሰውን እንዲያስተዳድር አልተፈጠረም። Man was not created to rule.
የሰው ልጆች ሌሎችን ለማስተዳደር ወይም ችግሮቻቸውን ለመፍታት የሚያደርጉት ሙከራ የማይሳካላቸው ለዚህ ነው። That is why human efforts have failed.
እስቲ ይህን አስብ፦ ብሪታኒካ አካደሚክ የተባለ የማመሣከሪያ ጽሑፍ እንደገለጸው የየትኛውም አገር መንግሥት ብቻውን በሚያደርገው ጥረት የሰው ልጆች የጋራ ጠላት የሆኑትን ድህነትን፣ ረሃብን፣ በሽታን፣ የተፈጥሮ አደጋን፣ ጦርነትንና ዓመፅን ማስወገድ ; የሚችል አይመስልም። Consider: British Academy No government seems to be able to eradicate poverty, hunger, disease, natural disasters, war, and violence; the common enemy of mankind.
የማመሣከሪያ ጽሑፉ አክሎ እንዲህ ብሏል፦ አንዳንዶች . . . The reference work adds: Some. . .
እነዚህን የሰው ልጆች ችግሮች በመዋጋት ረገድ ስኬታማ መሆን የሚቻለው ዓለም በአንድ መንግሥት ከተዳደረች ብቻ ነው ብለው ያምናሉ። ; They believe that the only solution to mankind's problems lies in a world government.  ;
ሆኖም የዓለም መንግሥታት በሙሉ ተዋህደው አንድ መንግሥት ቢሆኑ እንኳ ዓለም የምትተዳደረው ፍጹም ባልሆኑ የሰው ልጆች እስከሆነ ድረስ ከላይ የተጠቀሱትን ችግሮች ማስወገድ አይችሉም። But even if all the governments of the world were to unite in one world, they would not be able to solve the problems mentioned above, as long as they were ruled by imperfect humans.
ዓለም አቀፍ ችግሮችን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የማስወገድ ችሎታ ያለው የአምላክ መንግሥት ብቻ ነው። Only God's Kingdom has the power to eliminate world problems once and for all.
ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ ከሚናገረው ሐሳብ እንደምንረዳው፣ ጥሩ ሰዎች የዓለምን ፍጻሜ ወይም አሁን ያለው ክፉ ሥርዓት የሚጠፋበትን ጊዜ የሚፈሩበት ምክንያት የለም። According to the Bible, therefore, good people have no reason to fear the end of the world or the end of the present wicked system of things.
እንዲያውም በጉጉት የሚጠብቁት ጊዜ ነው፤ ምክንያቱም ይህ ብልሹ አሮጌ ዓለም አምላክ በሚያመጣው አስደናቂ አዲስ ዓለም የሚተካበት ጊዜ ነው። In fact, they look forward to it, Because this wicked system of things will soon be replaced by God's wonderful new world.
ታዲያ ይህ የሚሆነው መቼ ነው? When will this happen?
ቀጣዩ ርዕስ መጽሐፍ ቅዱስ ለዚህ ጥያቄ የሚሰጠውን መልስ ይዟል። The next article will consider the Bible's answer to that question.