Jump to content

decay

ከWiktionary
  1. ንጥፈት፤ የጨረር-ቀዳገል ግብታዊ ውልጠት ሂደት ነው። የኣንድ ጨረርገባሪ ጥጥቅ ገባሪነት ሂደት መልክ መንጠፍ ነው። (ከመመንመን ጋር ያነጻፅሯል)።
  2. መንጠፍ የኣንድ ጨረርገባሪ ጥጥቅ ገባሪነት ማብቃት ነው።
  3. መመንመን

የኣንድ ጨረርገባሪ ዕቅ (ቁስ) ገባሪነት ቅንሰት ነው። (ከመንጠፍ ጋር ያነጻጽሯል)። በኣንድ ውላጤ ውስጥ ያለፈ ጥጥቅ ያንን ሂደት የማይደግም በመሆኑ ምክንያት ያንን ጥጥቅ ለዚያ ዓይነት ሂደት ነጠፈ እንለዋለን። ተከታይ ውላጤ ካስፈለገው ከመጀመሪያው ውላጤ ፍጹም በተለየ የውላጤ ሂደት የሚከናወን ይሆናል። የጥጥቃን ንጥፈት ሂደት በቀጠለ ቁጥር በቁሱ ውስጥ ያሉት የዚያ ልዩ ውላጤ ሂደት ገባሪ ጥጥቃን ቁጥር በተብራራው የንጥፈት ስርዓት ምክንያት እየቀነሰ ይሄዳል። በዚህ ዓይነት የቁሱን ወይንም የዕቁን ጨረርገባሪነት እየመነመነ መሄድ ኣስተውሎ መነመነ የሚለውን ቃል ለጨረርገባሪ ቁሱ ወይንም ለጨረርገባሪ ዕቁ መጠቀም እጅግ ጠቃሚ በመሆኑ ምክንያት በጥጥቅ ደረጃ ሲሆን ነጠፈ እንዲሁም በቁስ መልክ ሲሆን መነመነ እንላለን። [1]

  1. እምሩ ታደሰ "ሕይወት ከጨረር ጋር"