ውስድ-ኣቻ ስርግውስድን ኣያሌ ዓይነት የሚያዮኑ ጨረሮች በኅብረሕዋስ ውስጥ ጉዳት የሚያመጡበትን ቅልጥፍና በሚያገናዝብ ኣብዢ ቁጥር ተባዝቶ የሚገኝ የኣኃዝ መጠን ነው። መስፈርቱ ሲቨርት ሲሆን ምልክቱም ‘ሲቨ’ ነው። ብዙውን ጊዜ የጋማ-ጨረሮች፣ የራጅ-ጨረሮችና የቤትኑሶች ኣብዢ ቁጥር 1 ሲሆን ለኣልፍኑሶች ግን 20 ነው።[1]